ዘኍል 22:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በሬዎችንና በጎችን አርዶ ወደ በለዓም፥ ከእርሱም ጋር ወዳሉት አለቆች ላከ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባላቅም ከብቶችና በጎች ሠዋ፤ ከፊሉንም ለበለዓምና ከርሱ ጋራ ለነበሩት አለቆች ሰጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም በሬዎችንና በጎችን አርዶ ወደ በለዓም ከእርሱም ጋር ወዳሉት ሹማምንት ላከ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም ባላቅ፥ ከብቶችና በጎች አሳርዶ ከሥጋው ጥቂቱን አብረውት ለነበሩት መሪዎችና ለበለዓም ሰጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም በሬዎችንና በጎችን አርዶ ወደ በለዓም ከእርሱም ጋር ወዳሉት አለቆች ላከ። |
በሜዳ ወደ ተገነባ ግንብ ራስ ላይም ወሰደው፤ አዞረውም፤ ሰባትም መሠዊያዎች ሠራ፤ በየመሠዊያውም ላይ አንድ ወይፈን፥ አንድም አውራ በግ አሳረገ።