እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፤ ከነዓናውያንንም አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ እነርሱንም፥ ከተሞቻቸውንም ሕርም ብለው አጠፉአቸው፤ የዚያን ስፍራ ስም “ሕርም” ብለው ጠሩት።
ዘኍል 22:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞሬዎናውያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የሴፎር ልጅ ባላቅ፣ እስራኤል በአሞራውያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራውያን ላይ ያደረገውን ሁሉ አየ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሞአብ ንጉሥ የጺጶር ልጅ ባላቅ እስራኤላውያን በአሞራውያን ላይ ያደረሱትን ጒዳት አየ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሴፎር ልጅ ባላቅ እስራኤል በአሞራውያን ላየ ያደረገውን ሁሉ አየ። |
እግዚአብሔርም የእስራኤልን ድምፅ ሰማ፤ ከነዓናውያንንም አሳልፎ በእጃቸው ሰጣቸው፤ እነርሱንም፥ ከተሞቻቸውንም ሕርም ብለው አጠፉአቸው፤ የዚያን ስፍራ ስም “ሕርም” ብለው ጠሩት።
የሞዓብም ንጉሥ የሴፎር ልጅ ባላቅ ተነሥቶ ከእስራኤል ጋር ተዋጋ፤ እንዲረግማችሁም የቢዖርን ልጅ በለዓምን ልኮ አስጠራው።
ወይስ ዛሬ ከሞዓብ ንጉሥ ከሴፎር ልጅ ከባላቅ አንተ ትሻላለህን? ወይስ እርሱ ከእስራኤል ጋር ተጣላን? ወይስ ተዋጋውን?