ዘኍል 2:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተቈጠሩ ሠራዊቱም፥ ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰራዊቱም ብዛት ሠላሳ ዐምስት ሺሕ አራት መቶ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእነርሱም ብዛት ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሠራዊቱም፥ ከእነርሱም የተቈጠሩ ሠላሳ አምስት ሺህ አራት መቶ ነበሩ። |
ከኤፍሬም ሰፈር የተቈጠሩ ሁሉ በየሠራዊቶቻቸው መቶ ስምንት ሺህ አንድ መቶ ነበሩ። እነርሱም ሦስተኛ ሆነው ይጓዛሉ።
እነዚህ የኤፍሬም ልጆች ወገኖች ናቸው፤ ከእነርሱም የተቈጠሩት ሠላሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ነበሩ። በየወገናቸው የዮሴፍ ልጆች እነዚህ ናቸው።
በዚያም ቀን ከየከተማው የመጡ የብንያም ልጆች ተቈጠሩ፤ ቍጥራቸውም ከገባዖን ሰዎች ሌላ ሃያ አምስት ሺህ ሰይፍ የሚመዝዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከገባዖንም ሰባት መቶ የተመረጡ ሰዎች ተቈጠሩ፤