La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 18:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ለሌ​ዋ​ው​ያን እን​ዲህ ብለህ ንገ​ራ​ቸው፦ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእ​ና​ንተ ርስት አድ​ርጌ የሰ​ጠ​ኋ​ች​ሁን ዐሥ​ራት በተ​ቀ​በ​ላ​ችሁ ጊዜ፥ እና​ን​ተ​ም​ከ​እ​ርሱ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ አድ​ር​ጋ​ችሁ የዐ​ሥ​ራት ዐሥ​ራት ታቀ​ር​ባ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ሌዋውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ርስት አድርጌ የምሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፣ እናንተም ካገኛችሁት ላይ አንድ ዐሥረኛ በማውጣት ለእግዚአብሔር መባ አድጋችሁ ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ለሌዋውያን ተናገር እነርሱንም እንዲህ በላቸው፦ ‘ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን አሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ለጌታ ለስጦታ የሚቀርበውን ቁርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘እግዚአብሔር ድርሻችሁ አድርጎ የሚሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፥ እናንተም በበኩላችሁ ከዚያው ከተቀበላችሁት የዐሥራት ዐሥራት በማውጣት ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጋችሁ አቅርቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሌዋውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእስራኤል ልጆች ለእናንተ ርስት አድርጌ የሰጠኋችሁን አሥራት በተቀበላችሁ ጊዜ፥ ለእግዚአብሔር ለማንሣት ቍርባን የአሥራት አሥራት ታቀርባላችሁ።

Ver Capítulo



ዘኍል 18:26
7 Referencias Cruzadas  

ሌዋ​ው​ያ​ኑም ዐሥ​ራ​ቱን በተ​ቀ​በሉ ጊዜ የአ​ሮን ልጅ ካህኑ ከሌ​ዋ​ው​ያን ጋር ይሁን፤ ሌዋ​ው​ያ​ኑም የዐ​ሥ​ራ​ቱን ዐሥ​ራት ወደ አም​ላ​ካ​ችን ቤት ወደ ጓዳ​ዎች ወደ ዕቃ ቤት ያም​ጡት።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና የሌዊ ልጆ​ችም የእ​ህ​ሉ​ንና የወ​ይ​ኑን፥ የዘ​ይ​ቱ​ንም ቀዳ​ም​ያት፥ የመ​ቅ​ደ​ሱን ዕቃ​ዎ​ችና የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉት ካህ​ናት፥ በረ​ኞ​ቹና መዘ​ም​ራኑ ወዳ​ሉ​ባ​ቸው ጓዳ​ዎች ያግ​ቡት፤ እን​ዲ​ሁም የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንን ቤት ከቶ አን​ተ​ውም።


መጀ​መ​ሪ​ያም ከም​ታ​ደ​ር​ጉት ሊጥ የተ​ለየ ቍር​ባን እስከ ልጅ ልጃ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ጣ​ላ​ችሁ።


“ለሌ​ዊም ልጆች እነሆ፥ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን አገ​ል​ግ​ሎት ስለ​ሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ዐሥ​ራት ርስት አድ​ርጌ ሰጥ​ቻ​ቸ​ዋ​ለሁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


መባ​ች​ሁም እንደ እህል ዐው​ድ​ማው ስን​ዴና እንደ ወይን መጭ​መ​ቂ​ያው ፍሬ ይቈ​ጠ​ር​ላ​ች​ኋል።


ከሌዊ ልጆ​ችም፥ ክህ​ነ​ትን የሚ​ቀ​በ​ሉት ከሕ​ዝቡ ማለት ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው፥ እነ​ርሱ ምንም ከአ​ብ​ር​ሃም ወገብ ቢወጡ ከእ​ነ​ርሱ ዐሥ​ራ​ትን በሕግ እን​ዲ​ያ​ስ​ወጡ ትእ​ዛዝ አላ​ቸው።