የእህሉን ቍርባንና የኀጢአትን መሥዋዕት የንስሓንም መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም ዘንድ እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።
ዘኍል 18:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤል ልጆች ዘንድ የተከለከለው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለእግዚአብሔር ፈጽሞ የተሰጠ በእስራኤል ያለ ማንኛውም ነገር ሁሉ የአንተ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤል ዘንድ እርም የሆነው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በእስራኤል ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለእኔ የተለየ ነገር ሁሉ ለእናንተ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤል ዘንድ እርም የሆነው ሁሉ ለአንተ ይሆናል። ከሰው ወይም ከእንስሳ ቢሆን፥ |
የእህሉን ቍርባንና የኀጢአትን መሥዋዕት የንስሓንም መሥዋዕት ይበላሉ፤ በእስራኤልም ዘንድ እርም የሆነው ነገር ሁሉ ለእነርሱ ይሆናል።
“ለእግዚአብሔርም የተለየ እርም የሆነ ነገር ሁሉ፥ ሰው ቢሆን ወይም እንስሳ ወይም የርስቱ እርሻ ቢሆን፥ አይሸጥም፤ አይቤዥም፤ እርም የሆነ ነገር ሁሉ ለእግዚአብሔር ቅዱሰ ቅዱሳን ነው።