ዘኍል 14:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም አቤቱ፥ ኀይልህ ይገለጥ፤ እንዲህ ብለህ እንደ ተናገርህ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “አሁንም እንዲህ ስትል በተናገርኸው መሠረት የጌታ ኀይል ይገለጥ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም፥ እባክህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን፤ አንተም እንዲሁ ቃል ኪዳን ያደረግከው እንዲህ ብለህ በተነናገርህ ጊዜ ነው፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ጌታ ሆይ፥ ኀይልህን እንድታሳየን እለምንሃለሁ፤ ደግሞም እንዲህ ስትል የተናገርከውን የተስፋ ቃል ፈጽምልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፥ እባክህ፦ እግዚአብሔር ታጋሽና ምሕረቱ የበዛ፥ አበሳንና መተላለፍን ይቅር የሚል፥ ኃጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኃጢአት እስከ ሦስትና እስከ አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው ብለህ እንደ ተናገርህ፥ የጌታ ኃይል ታላቅ ይሁን። |
እግዚአብሔር ‘እነዚህን ሕዝብ ወደ ማለላቸው ምድር ያገባቸው ዘንድ አልቻለምና በምድረ በዳ ገደላቸው’ ብለው ይናገራሉ።
እግዚአብሔር መዓቱ የራቀ ምሕረቱ የበዛ ጻድቅ፥ አበሳን፥ መተላለፍንና ኀጢአትን ይቅር የሚል፥ ኀጢአተኞችንም ከቶ የማያነጻ፥ የአባቶችን ኀጢአት እስከ ሦስትና አራት ትውልድ ድረስ በልጆች ላይ የሚያመጣ ነው።
ነገር ግን በምድር ላይ ኀጢአትን ያስተሰርይ ዘንድ ለሰው ልጅ ሥልጣን እንዳለው እንድታውቁ፤” በዚያን ጊዜ ሽባውን “ተነሣ፤ አልጋህን ተሸከምና ወደ ቤትህ ሂድ፤” አለው።