የሚኖሩባትም ምድር መልካም ወይም ክፉ፥ የሚኖሩባቸውም ከተሞች ቅጥር ያላቸው ወይም የሌላቸው እንደ ሆኑ፥
የሚኖሩባት ምድር ምን ዐይነት ናት? መልካም ወይስ መጥፎ? የሚኖሩባቸውስ ከተሞች ምን ይመስላሉ? በግንብ ያልታጠሩ ናቸው ወይስ የተመሸጉ?
እንዲሁም የሚኖሩባት ምድር መልካም ወይም ክፉ፥ የሚኖሩባቸውም ከተሞች ሰፈሮች ወይም የተመሸጉ አምባዎች እንደ ሆኑ፥
ምድሪቱ መልካም ወይም መጥፎ እንደ ሆነች፥ ሕዝቡም የሚኖሩት ግልጥ በሆኑ መንደሮች ወይም በተመሸጉ ከተሞች እንደ ሆነ አጥኑ።
ጥቂቶች ወይም ብዙዎች እንደ ሆኑ፥ የሚኖሩባትም ምድር መልካም ወይም ክፉ፥ የሚኖሩባቸውም ከተሞች ሰፈሮች ወይም አምቦች እንደ ሆኑ፥
ከግብፃውያንም እጅ አድናቸው ዘንድ፥ ከዚያችም ሀገር ወተትና ማር ወደምታፈስሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊዪቱና ወደ መልካሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነዓናውያንም፥ ወደ ኬጤዎናውያንም፥ ወደ አሞሬዎናውያንም፥ ወደ ፌርዜዎናውያንም፥ ወደ ጌርጌሴዎናውያንም፥ ወደ ኤዌዎናውያንም፥ ወደ ኢያቡሴዎናውያንም ስፍራ አወጣቸው ዘንድ ወረድሁ።
ምድሪቱንም እንዴት እንደ ሆነች፥ በእርስዋም የሚኖሩ ሰዎች ብርቱዎች ወይም ደካሞች፥ ጥቂቶች ወይም ብዙዎች እንደ ሆኑ፥
ምድሪቱም ለም ወይም ጠፍ፥ ዛፍ ያለባት ወይም የሌለባት እንደ ሆነች አይታችሁ፥ ከምድሪቱ ፍሬ አምጡ፤” ወራቱም ወይኑ አስቀድሞ ፍሬ የሚያፈራበት ነበረ።