ዘኍል 11:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ሁሉ፥ በሌሊትም ሁሉ፥ በነጋውም ሁሉ ሕዝቡ ተነሥተው ድርጭትን ሰበሰቡ፤ ከሁሉ ጥቂት የሰበሰበ ዐሥር የቆሮስ መስፈሪያ ያህል ሰበሰበ፤ በሰፈሩም ዙሪያ ሁሉ አስጥተው አደረቁት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ዕለት ቀንና ሌሊቱን በሙሉ፣ በማግስቱም ሙሉውን ቀን እንደዚሁ ሕዝቡ ወጥቶ ድርጭቶች ሰበሰበ፤ ከዐሥር የቆሮስ መስፈሪያ ያነሰ የሰበሰበ ማንም አልነበረም፤ የሰበሰቡትንም በሰፈሩ ዙሪያ ሁሉ አሰጡት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን ሁሉ በሌሊትም ሁሉ በማግስቱም ሁሉ ሕዝቡ ተነሥተው ድርጭትን ሰበሰቡ፤ ከሁሉ ጥቂት የሰበሰበ ዐሥር የቆሮስ መስፈሪያ የሚህል ሰበሰበ፤ በሰፈሩም ዙሪያ ሁሉ አሰጡት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ በዚያን ቀንና ሌሊት፥ እንዲሁም በማግስቱ ሕዝቡ ድርጭት እያሳደዱ በመያዝ ደከሙ፤ ከዐሥር ኪሎ ግራም ያነሰ የሰበሰበ አልነበረም፤ እንዲደርቁም በሰፈር ዙሪያ አሰጡአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ሁሉ በሌሊትም ሁሉ በነጋውም ሁሉ ሕዝቡ ተነሥተው ድርጭትን ሰበሰቡ፤ ከሁሉ ጥቂት የሰበሰበ አሥር የቆሮስ መስፈሪያ የሚህል ሰበሰበ፤ በሰፈሩም ዙሪያ ሁሉ አሰጡት። |
እንዲሁም የኢፍና የባዶስ መስፈሪያ አንድ ይሁን፤ የባዶስ መስፈሪያ፥ የቆሮስ መስፈሪያ ዐሥረኛ ክፍል፥ የኢፍ መስፈሪያውም የቆሮስ መስፈሪያ ዐሥረኛ ክፍል ይሁን። መስፈሪያው እንደ ቆሮስ መስፈሪያ ይሁን።