ዘኍል 11:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም እያንዳንዳቸው በየወገናቸው በድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ እግዚአብሔርም እጅግ ተቈጣ፤ ነገሩም በሙሴ ፊት ክፉ ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴ፣ ሕዝቡ ሁሉ በየቤተ ሰቡ፣ በየድንኳኑ ደጃፍ ሆኖ ሲያለቅስ ሰማ። እግዚአብሔርም እጅግ ተቈጣ፤ ሙሴም ተጨነቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም ሕዝቡ በየወገኑ፥ ሰው ሁሉ በየድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ የጌታም ቁጣ እጅግ ነደደ፤ ሙሴም በጣም ቅር ተሰኘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡ ሁሉ በየድንኳኖቻቸው ደጃፍ ላይ በየቤተሰባቸው ቆመው ሲያለቅሱ ሙሴ ሰማቸው፤ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ተቈጥቶ ስለ ነበረ ሙሴ በጣም ተጨነቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም ሕዝቡ በወገኖቻቸው፥ ሰው ሁሉ በድንኳኑ ደጃፍ፥ ሲያለቅሱ ሰማ፤ የእግዚአብሔርም ቍጣ እጅግ ነደደ፤ ሙሴም ተቈጣ። |
ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በሕዝቡ ላይ ታላቅ ቍጣን ተቈጣ፤ እጁንም በላያቸው ዘርግቶ መትቶአቸዋል፤ ተራሮችም ተንቀጠቀጡ፤ ሬሳቸውም በመንገድ መካከል እንደ ጕድፍ ሆኖአል። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።
አንተም የሰጠሁህን ርስት ትለቅቃለህ፤ ለዘለዓለምም በማታውቃት ምድር ለጠላቶችህ አስገዛሃለሁ፤ ቍጣዬ ለዘለዓለም እንደ እሳት ትነድዳለችና።
ሕዝቡም በክፋት በእግዚአብሔር ፊት አጕረመረሙ፤ እግዚአብሔርም ሰምቶ ተቈጣ፤ እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ በእነርሱ ላይ ነደደች፤ ከሰፈሩም አንዱን ወገን በላች።
ሙሴም እግዚአብሔርን አለው፥ “ለምን በአገልጋይህ ላይ ክፉ አደረግህ? ለምንስ በፊትህ ሞገስን አላገኘሁም? ለምንስ የዚህን ሁሉ ሕዝብ ሸክም በእኔ ላይ አደረግህ?
ከቆሬ ድንኳን ዙሪያም ሁሉ ፈቀቅ አሉ፤ ዳታንና አቤሮንም ከሴቶቻቸው፥ ከልጆቻቸውና ከጓዛቸው ጋር ወጥተው በድንኳኖቻቸው ደጃፍ ቆሙ።
ሕዝቡም፥ “በምድረ በዳ እንሞት ዘንድ ከግብፅ ለምን አወጣኸን?” ብለው እግዚአብሔርንና ሙሴንም አሙ። “እንጀራ የለም፤ ውኃም የለምና፥ ሰውነታችንም ይህን ጥቅም የሌለው እንጀራ ተጸየፈች” ብለው ተናገሩ።
እሳት ከቍጣዬ ትነድዳለችና፥ እስከ ሲኦል ድረስ ታቃጥላለች፤ ምድርንም ከፍሬዋ፤ ጋር ትበላለች፤ የተራሮችን መሠረት ታነድዳለች።