ነህምያ 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፥ “ሁላችሁ ከብላቴኖቻችሁ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ እደሩ፤ በሌሊትም ጠባቂዎች ሁኑልን፤ በቀንም ሥሩ” አልኋቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ለሕዝቡ፣ “ሌሊት ዘብ በመጠበቅና ቀን ሥራ በመሥራት እንዲያገለግለን እያንዳንዱ ሰው ከነረዳቱ በኢየሩሳሌም ይቈይ” አልኋቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህን ጊዜ የሥራ ኀላፊዎቹን “በሌሊት ከተማይቱን ለመጠበቅ፥ ቀን ሥራችንን ያለ ሥጋት ለመሥራት እንችል ዘንድ እናንተም ሆናችሁ ረዳቶቻችሁ፥ ሌሊት ሌሊት በኢየሩሳሌም ቈዩ” አልኳቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፦ ሁላችሁ ከብላቴኖቻችሁ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ እደሩ፥ በሌሊትም ጠባቂዎች ሁኑልን፥ በቀንም ሥሩ አልኋቸው። |
እኔና ወንድሞችም፥ ብላቴኖችም በኋላዬም የነበሩት ጠባቂዎች ልብሳችንን አናወልቅም ነበር። ወደ ውኃም ስንሄድ መሣሪያችንን እንደታጠቅን እንሄድ ነበር።