የቀንደ መለከቱን ድምፅ ወደምትሰሙበት ስፍራ ወደዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል” አልኋቸው።
ነህምያ 4:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥራውንም እንሠራ ነበር፤ ከማለዳ ወገግታም ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ እኩሌቶቹ ጦር ይይዙ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጎሕ ሲቀድ ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ እኩሌቶቹ ሰዎች ጦራቸውን እንደ ያዙ ሥራውን ቀጠልን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም በየቀኑ ከማለዳ ጀምሮ በምሽት፥ ከዋክብት እስከሚወጡበት ጊዜ ድረስ እኩሌቶቹ ሲሠሩ፥ እኩሌቶቹ መሣሪያ ታጥቀው ዘብ በመቆም ይጠብቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥራውንም ሠራን ከማለዳ ወገግታም ጀምሮ ከዋክብት እስኪወጡ ድረስ እኩሌቶቹ ጦር ይይዙ ነበር። |
የቀንደ መለከቱን ድምፅ ወደምትሰሙበት ስፍራ ወደዚያ ወደ እኛ ተሰብሰቡ፤ አምላካችን ስለ እኛ ይዋጋል” አልኋቸው።
ደግሞም በዚያ ጊዜ ሕዝቡን፥ “ሁላችሁ ከብላቴኖቻችሁ ጋር በኢየሩሳሌም ውስጥ እደሩ፤ በሌሊትም ጠባቂዎች ሁኑልን፤ በቀንም ሥሩ” አልኋቸው።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን እኔ ባለሁበት አለሁ፤ ለእኔም የሰጠኝ ጸጋው ለከንቱ የሆነብኝ አይደለም፤ እኔም ከሁሉ ይልቅ ደከምሁ፤ ነገር ግን በእኔ ላይ ያደረው የእግዚአብሔር ጸጋ አጸናኝ እንጂ እኔ አይደለሁም።
አሁንም የተወደዳችሁ ወንድሞቻችን ሆይ፥ የጸናችሁና የማትናወጡ ሁኑ፤ ዘወትር በጎ ምግባርን አብዝታችሁ ለእግዚአብሔር አበርክቱ፤ ስለ ጌታችን መድከማችሁ ለከንቱ እንዳይደለ ታውቃላችሁና።