ከቅጥሩም በስተኋላ በኩል ባለው በታችኛው ክፍል በሰዋራ ስፍራ ሰይፋቸውንና ጦራቸውን፥ ቀስታቸውንም አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኋቸው፤
ነህምያ 4:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አናጢዎቹም ሁሉ እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፤ ቀንደ መለከትም የሚነፋ በአጠገቤ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱም ግንበኛ ቅጥሩን በሚሠራበት ጊዜ ሰይፉን በወገቡ ላይ ታጥቆ ነበር፤ መለከት የሚነፋው ሰው ግን ከእኔ አይለይም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱም ግንበኛ ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፤ እምቢልታ ነፊውም ከአጠገቤ አይለይም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አናጢዎቹም ሁሉ እያንዳንዱ ሰይፉን በወገቡ ታጥቆ ይሠራ ነበር፥ ቀንደ መለከትም የሚነፋ በአጠገቤ ነበረ። |
ከቅጥሩም በስተኋላ በኩል ባለው በታችኛው ክፍል በሰዋራ ስፍራ ሰይፋቸውንና ጦራቸውን፥ ቀስታቸውንም አስይዤ ሕዝቡን በየወገናቸው አቆምኋቸው፤
ቅጥሩንም የሚሠሩትና ሸክም ተሸካሚዎቹ በአንድ እጃቸው ይሠሩ ነበር፤ በአንድ እጃቸውም የጦር መሣሪያቸውን ይይዙ ነበር።
ታላላቆቹንና ሹሞቹን፥ የቀሩትንም ሕዝብ፥ “ሥራው ታላቅና ሰፊ ነው፤ እኛም በቅጥሩ ላይ ተበታትነናል፤ አንዱም ከሁለተኛው ርቆአል፤
በሚገፋችሁም ጠላት ላይ በምድራችሁ ወደ ሰልፍ ስትወጡ በምልክት መለከቶችን ንፉ፤ በእግዚአብሔርም በአምላካችሁ ፊት ትታሰባላችሁ፤ ከጠላቶቻችሁም ትድናላችሁ።