ነህምያ 3:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከፈረሶች በር በላይ ካህናቱ እያንዳንዳቸው በየቤታቸው አንጻር ሠሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የፈረስ በር ተብሎ ከሚጠራው በላይ ያለውን ደግሞ ካህናቱ እያንዳንዳቸው በየመኖሪያ ቤታቸው ትይዩ ያለውን መልሰው ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከ “የፈረሶች በር” በላይ ጀምሮ በየቤታቸው ትይዩ ያለውን ካህናቱ እያንዳንዳቸው አደሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌሎች ካህናትም እያንዳንዳቸው በየመኖሪያ ቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን መስመር በመከተል ከፈረስ ቅጽር በር በስተሰሜን በኩል ያለውን ክፍል ሠሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከፈረሱ በር በላይ ካህናቱ እያንዳንዳቸው በየቤታቸው አንጻር አደሱ። |
ከእነርሱም በኋላ ብንያምና አሴብ በቤታቸው አንጻር ያለውን ሠሩ። ከእነርሱም በኋላ የሐናንያ ልጅ የመዓስያ ልጅ ዓዛርያስ በቤቱ አጠገብ ያለውን ሠራ።
ከዚያም በኋላ የሄሜር ልጅ ሳዶቅ በቤቱ አንጻር ያለውን ሠራ። ከእርሱም በኋላ የምሥራቁ በር ጠባቂ የሴኬንያ ልጅ ሰማያ ሠራ።
የአስሬሞትም ሸለቆ ሁሉ እስከ ቄድሮን ወንዝ ድረስ በምሥራቅ በኩል እስካለው እስከ ፈረስ በር ማዕዘን ድረስ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ከእንግዲህም ወዲህ ለዘለዓለም አይነቀልም፤ አይፈርስምም።