ነህምያ 11:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእስራኤልም የቀሩት ከካህናትና ከሌዋውያንም እያንዳንዳቸው በየርስታቸው በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀሩት እስራኤላውያንም ከካህናቱና ከሌዋውያኑ ጋራ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ በየርስታቸው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእስራኤል የቀሩት ካህናቱና ሌዋውያኑ እያንዳንዱ በየርስቱ በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በተረፈ ሌሎቹ እስራኤላውያን፥ ካህናትና ሌዋውያን በየርስታቸው በሌሎቹ የይሁዳ ከተሞችና መንደሮች ይኖሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእስራኤልም የቀሩት ከካህናትና ከሌዋውያንም እያንዳንዳቸው በየርስታቸው በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ነበሩ። |
በኢየሩሳሌምም የተቀመጡት የሀገሩ አለቆች እነዚህ ናችው፤ እስራኤል ግን ካህናቱም፥ ሌዋውያኑም፥ ናታኒምም፥ የሰሎሞንም አገልጋዮች ልጆች እያንዳንዳቸው በየርስታቸውና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ተቀመጡ።