ሚክያስ 7:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፥ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፥ እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብ ያያሉ፣ ያፍራሉም፤ ኀይላቸውን ሁሉ ያጣሉ፤ አፋቸውን በእጃቸው ይይዛሉ፤ ጆሯቸውም ትደነቍራለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሕዛብ ያያሉ፥ በኀይላቸው ሁሉ ያፍራሉ፤ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮዎቻቸውም ይደነቁራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይል ያላቸው ቢሆኑም ይህን አይተው ያፍራሉ፤ እጆቻቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፤ ጆሮዎቻቸውንም ይደፍናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሕዛብ አይተው በጕልበታቸው ሁሉ ያፍራሉ፥ እጃቸውን በአፋቸው ላይ ያኖራሉ፥ ጆሮአቸውም ትደነቍራለች፥ እንደ እባብም መሬት ይልሳሉ፥ |
“አንተ ስታስተምረኝ እኔ የምመልሰው ምን አለኝ? ይህንስ እየሰማሁ ከእግዚአብሔር ጋር እከራከር ዘንድ እኔ ምንድን ነኝ? እጄን በአፌ ላይ ከማኖር በቀር የምመልሰው ምንድን ነው?
በማለዳ መገሥገሣችሁም ከንቱ ነው። ለወዳጆቹ እንቅልፍን በሰጠ ጊዜ፥ እናንተ የመከራን እንጀራ የምትበሉ፥ ከተቀመጣችሁበት ተነሡ።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና።
“ሥራቸውንና አሳባቸውን ዐውቄአለሁ፤ እነሆም እኔ እመጣለሁ፤ አሕዛብንና ልሳናትንም ሁሉ እሰበስባለሁ፤ እነርሱም ይመጣሉ፤ ክብሬንም ያያሉ።
ታላቅ እሆናለሁ፤ እቀደስማለሁ፤ እመሰገናለሁም፤ በብዙ አሕዛብም ዐይን የታወቅሁ እሆናለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ያውቃሉ።
በዱር አራዊትም መካከል እንዳለ አንበሳ፥ በበጎች መንጋም መካከል አልፎ እንደሚረግጥ፥ የሚታደግም ሳይኖር እንደሚነጥቅ እንደ አንበሳ ደቦል፥ እንዲሁ የያዕቆብ ቅሬታ በአሕዛብና በብዙ ወገኖች መካከል ይሆናል።
የመንግሥታትንም ዙፋን እገለብጣለሁ፥ የአሕዛብንም መንግሥታት ኃይል አጠፋለሁ፣ ሰረገሎችንና የሚቀመጡባቸውንም እገለብጣለሁ፣ ፈረሶችና ፈረሰኞቻቸውም እያንዳንዳቸው በወንድማቸው ሰይፍ ይወድቃሉ።
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።
አሕዛብም ተቈጡ፤ ቍጣህም መጣ፤ በሙታንም ትፈርድ ዘንድ ዘመን መጣ፤ ለባሪያዎችህም ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚፈሩት ለታናናሾችና ለታላላቆችም ዋጋቸውን ትሰጥ ዘንድ፥ ምድርንም የሚያጠፉትን ታጠፋ ዘንድ ዘመን መጣ።”