የእግዚአብሔርንም ስም ጠርቶ የሚሰድብ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የሀገር ልጅ ቢሆን፥ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ቢሳደብ ይገደል።
ማቴዎስ 9:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም ከጻፎቹ አንዳንዶቹ በልባቸው “ይህስ ይሳደባል፤” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ የአይሁድ ሃይማኖት መምህራን፣ “ይህማ እግዚአብሔርን መሳደብ ነው” በማለት በልባቸው አጕረመረሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆ ከጻፎች አንዳንዶቹ በልባቸው “ይህስ ይሳደባል፤” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ጊዜ አንዳንድ የሕግ መምህራን፥ “ይህ ሰው በእግዚአብሔር ላይ የስድብ ቃል ይናገራል!” እያሉ በልባቸው አሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ከጻፎቹ አንዳንዱ በልባቸው፦ ይህስ ይሳደባል አሉ። |
የእግዚአብሔርንም ስም ጠርቶ የሚሰድብ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል፤ ማኅበሩም ሁሉ በድንጋይ ይውገሩት፤ መጻተኛ ወይም የሀገር ልጅ ቢሆን፥ የእግዚአብሔርን ስም ጠርቶ ቢሳደብ ይገደል።
የሀገር ልጅ ቢሆንም ወይም መጻተኛ ቢሆን፥ በእጁ ትዕቢትን የሚያደርግ ሰው እግዚአብሔርን ሰድቦአል፤ ያም ሰው ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጠፋል።
በዚያን ጊዜ ሊቀ ካህናቱ ልብሱን ቀዶ “ተሳድቦአል፤ እንግዲህ ወዲህ ምስክሮች ስለ ምን ያስፈልገናል? እነሆ፥ ስድቡን አሁን ሰምታችኋል፤ ምን ይመስላችኋል?” አለ።
ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “የሚሳደብ ይህ ማን ነው? ከአንዱ ከእግዚአብሔር በቀር ኀጢአትን ማስተስረይ ማን ይችላል?” ብለው ያስቡ ጀመር።