La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማቴዎስ 8:32 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ፤ በውሃም ውስጥ ሞቱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኢየሱስም፣ “ሂዱ!” አላቸው። አጋንንቱም ከሰዎቹ ወጥተው ዐሣማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ዐሣማዎቹም በሙሉ ከነበሩበት አፋፍ እየተጣደፉ ባሕሩ ውስጥ በመግባት ውሃው ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም “ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ወጥተው ወደ አሣማዎቹ ሄደው ገቡ፤ እነሆ የዓሣማዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር ሮጡ፥ በውኆቹ ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስም “ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህም ከሰዎቹ ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ሄዱና ገቡባቸው። ዐሣማዎቹም በሙሉ ከገደሉ አፋፍ ላይ እየተንደረደሩ ወርደው በባሕር ውስጥ ሰጥመው ሞቱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ በውኃም ውስጥ ሞቱ።

Ver Capítulo



ማቴዎስ 8:32
10 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ በምን ታስ​ተ​ዋ​ለህ? አለው፤ እር​ሱም ወጥቼ በነ​ቢ​ያቱ ሁሉ አፍ ሐሰ​ተኛ መን​ፈስ እሆ​ና​ለሁ አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ማሳ​ሳ​ትስ ታሳ​ስ​ተ​ዋ​ለህ፤ ይሆ​ን​ል​ሃ​ልም፤ ውጣ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርግ አለ።


አጋንንቱም “ታወጣንስ እንደሆንህ፥ ወደ እሪያው መንጋ ስደደን፤” ብለው ለመኑት። “ሂዱ፤” አላቸው።


እረኞችም ሸሹ፤ ወደ ከተማይቱም ሄደው ነገሩን ሁሉ አጋንንትም በአደሩባቸው የሆነውን አወሩ።


ኢየሱስም ፈቀደላቸው። ርኵሳን መናፍስቱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ገቡ፤ ሁለት ሺህም የሚያህል መንጋ ከአፋፉ ወደ ባሕር ተጣደፉና በባሕር ሰጠሙ።


እነ​ዚያ አጋ​ን​ን​ትም ከዚያ ሰው ላይ ወጥ​ተው ወደ እሪ​ያ​ዎች ገቡ፤ የእ​ሪ​ያ​ዎ​ችም መንጋ አብ​ደው ከገ​ደሉ ወደ ባሕር ጠል​ቀው ሞቱ።


እር​ሱ​ንም በተ​ወ​ሰ​ነው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምክ​ርና በቀ​ደ​መው ዕው​ቀቱ እና​ንተ አሳ​ል​ፋ​ችሁ በኃ​ጥ​ኣን እጅ ሰጣ​ች​ሁት፤ ሰቅ​ላ​ች​ሁም ገደ​ላ​ች​ሁት።


እጅ​ህና ምክ​ርህ እን​ዲ​ደ​ረግ የወ​ሰ​ኑ​ትን ይፈ​ጽሙ ዘንድ።


ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል፤