ማቴዎስ 8:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)32 እርሱም “ሂዱ” አላቸው፤ እነርሱም ወጥተው ወደ አሣማዎቹ ሄደው ገቡ፤ እነሆ የዓሣማዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር ሮጡ፥ በውኆቹ ውስጥ ሰጥመው ሞቱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም32 ኢየሱስም፣ “ሂዱ!” አላቸው። አጋንንቱም ከሰዎቹ ወጥተው ዐሣማዎቹ ውስጥ ገቡ፤ ዐሣማዎቹም በሙሉ ከነበሩበት አፋፍ እየተጣደፉ ባሕሩ ውስጥ በመግባት ውሃው ውስጥ ሰጥመው ሞቱ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም32 ኢየሱስም “ሂዱ!” አላቸው። ስለዚህም ከሰዎቹ ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ሄዱና ገቡባቸው። ዐሣማዎቹም በሙሉ ከገደሉ አፋፍ ላይ እየተንደረደሩ ወርደው በባሕር ውስጥ ሰጥመው ሞቱ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)32 እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ፤ በውሃም ውስጥ ሞቱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)32 እነርሱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ሄዱና ገቡ፤ እነሆም የእሪያዎቹ መንጋ ሁሉ ከአፋፉ ወደ ባሕር እየተጣደፉ ሮጡ በውኃም ውስጥ ሞቱ። Ver Capítulo |