ማቴዎስ 7:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምክንያቱም እንደ አይሁድ ሃይማኖት መምህራናቸው ሳይሆን እንደ ባለሥልጣን ያስተምራቸው ስለ ነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ጻፎቻቸው ሳይሆን፥ እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ስለ ነበረ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተደነቁትም እርሱ እንደ ሕግ መምህሮቻቸው ሳይሆን፥ እንደ ባለሥልጣን ያስተምራቸው ስለ ነበረ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደ ባለ ሥልጣን ያስተምራቸው ነበርና። |
የምናገረውን ቃል አውቅ ዘንድ ጌታ እግዚአብሔር የጥበብ ምላስን ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፤ ለመስማትም ጆሮን ሰጥቶኛል።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፤ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፤ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፤ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፤ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።