አሜስያስም የእግዚአብሔርን ሰው፥ “ለእስራኤል ጭፍራ የሰጠሁት መቶ መክሊት ምን ይሁን?” አለው። የእግዚአብሔርም ሰው፥ “ከዚህ አብልጦ ይሰጥህ ዘንድ ለእግዚአብሔር አይሳነውም” ብሎ መለሰለት።
ማቴዎስ 6:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ ‘ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ፣ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ “ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?” ብላችሁ አትጨነቁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ እያላችሁ በማሰብ አትጨነቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ፦ ምን እንበላለን? ምንስ እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን? ብላችሁ አትጨነቁ፤ |
አሜስያስም የእግዚአብሔርን ሰው፥ “ለእስራኤል ጭፍራ የሰጠሁት መቶ መክሊት ምን ይሁን?” አለው። የእግዚአብሔርም ሰው፥ “ከዚህ አብልጦ ይሰጥህ ዘንድ ለእግዚአብሔር አይሳነውም” ብሎ መለሰለት።
“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደክሚያለሽ፥ ትቸገሪያለሽም፤ ታዘጋጂያለሽም።
ወደ አደባባይ ወደ ሹሞቹና ወደ ነገሥታቱ፥ ወደ መኳንንቱም በሚወስዱአችሁ ጊዜ የምትሉትንና የምትናገሩትን አታስቡ።
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አላቸው፥ “ስለዚህ እላችህዋለሁ፤ ለነፍሳችሁ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት፥ ለሰውነታችሁም ስለምትለብሱት አትጨነቁ።