ማቴዎስ 6:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደግሞስ ስለ ልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ? እስኪ የሜዳ አበቦችን ተመልከቱ፤ አይለፉም፤ ወይም አይፈትሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ልብስስ ለምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ ተመልከቱ፤ አይለፉም አይፈትሉምም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞስ ስለ ልብስ ለምን ትጨነቃላችሁ? የአሸንድዬ አበቦች እንዴት እንደሚያድጉ እስቲ ተመልከቱ፤ እነርሱ በሥራ አይደክሙም፤ አይፈትሉም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ልብስስ ስለ ምን ትጨነቃላችሁ? የሜዳ አበቦች እንዴት እንዲያድጉ ልብ አድርጋችሁ ተመልከቱ፤ |
“ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ በምትበሉትና በምትጠጡት፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ፤ ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?
ጌታችን ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አላት፥ “ማርታ፥ ማርታ፥ በብዙ ነገር ትደክሚያለሽ፥ ትቸገሪያለሽም፤ ታዘጋጂያለሽም።
ወደ አደባባይ ወደ ሹሞቹና ወደ ነገሥታቱ፥ ወደ መኳንንቱም በሚወስዱአችሁ ጊዜ የምትሉትንና የምትናገሩትን አታስቡ።
ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አላቸው፥ “ስለዚህ እላችህዋለሁ፤ ለነፍሳችሁ ስለምትበሉትና ስለምትጠጡት፥ ለሰውነታችሁም ስለምትለብሱት አትጨነቁ።
እነሆ፥ አበባዎችን እንደሚያድጉ ተመልከቱ፤ አይፈትሉም፤ አይደክሙም፤ ነገር ግን እላችኋለሁ፤ ሰሎሞን እንኳ በክብሩ ዘመን ሁሉ ከእነርሱ እንደ አንዱ አልለበሰም።