ማቴዎስ 5:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እውነት እልሃለሁ፤ ካስፈረደብህ ግን የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከዚያ አትወጣም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእውነት እልሃለሁ፥ የተፈረደብህን የመጨረሻዋን ሳንቲም ከፍለህ እስክትጨርስ ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እውነት እልሃለሁ፥ የመጨረሻዋን ሳንቲም እስክትከፍል ድረስ ከቶ ከዚያ አትወጣም። |
ከባለጋራህ ጋር ወደ ሹም በምትሄድበት ጊዜ ወደ ዳኛ እንዳይወስድህ በመንገድ ሳለህ ታረቅ፤ ዕዳህንም ክፈል፤ ዳኛው ለሎሌው አሳልፎ ይሰጥሃልና። ሎሌውም በወኅኒ ቤት ያስርሃል።
ከዚህም ሁሉ ጋር ከዚህ ወደ እናንተ ማለፍ የሚሹ እንዳይችሉ፥ ከእናንተ ወገን የሆኑትም ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል አለ’
በዚያም ቀን በቅዱሳኑ ሊከብር ምስክርነታችንንም አምናችኋልና በሚያምኑት ሁሉ ዘንድ ሊደነቅ ሲመጣ፥ ከጌታ ፊት ከኀይሉም ክብር ርቀው በዘላለም ጥፋት ይቀጣሉ።