እርስዋም እንዲህ አለች፥ “የቀደሙ ሰዎች በእስራኤል ዘንድ አማኞች በሚያስቡት ነገር ተሳስተው እንደ ሆነ በአቤልና በዳን በእውነት ይጠይቁ ይባል ነበር፤ በርግጥም በዚህ ዐይነት ነገር ከተሳሳቱ በአቤል ይጠይቁ ነበር።
ማቴዎስ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለቀደሙት ‘አትግደል’ እንደተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ለቀደሙት ሰዎች፣ ‘አትግደል፤ የገደለ ይፈረድበታል’ እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለቀደሙት ‘አትግደል፥ የገደለ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል’ እንደተባለ ሰምታችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በቀድሞ ጊዜ ለነበሩ ሰዎች የተባለውን ሰምታችኋል፤ ይኸውም ‘አትግደል፤ ሰውን የገደለ ይፈረድበታል’ የሚል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለቀደሙት፦ አትግደል እንደ ተባለ ሰምታችኋል፤ የገደለም ሁሉ ፍርድ ይገባዋል። |
እርስዋም እንዲህ አለች፥ “የቀደሙ ሰዎች በእስራኤል ዘንድ አማኞች በሚያስቡት ነገር ተሳስተው እንደ ሆነ በአቤልና በዳን በእውነት ይጠይቁ ይባል ነበር፤ በርግጥም በዚህ ዐይነት ነገር ከተሳሳቱ በአቤል ይጠይቁ ነበር።
ነፍሰ ገዳዩ በማኅበሩ ፊት ለፍርድ እስከሚቆም ድረስ እንዳይሞት፥ ከተሞቹ ከደም ተበቃይ የመማፀኛ ከተሞች ይሁኑላችሁ።
“አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ በሀገርህ ደጅ ሁሉ በየነገዶችህ ፈራጆችንና መባውን የሚጽፉትን ሹሙ፤ ለሕዝቡም ቅን ፍርድን ይፍረዱ።