አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦
እንዲህም እያለ ያስተምራቸው ጀመር፤
አፉንም ከፍቶ እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፤
እንዲህ እያለም ያስተምራቸው ጀመር፤
ከዚያም በኋላ ኢዮብ አፉን ከፈተ፥ የተወለደባትንም ቀን ረገመ።
የተወደደች ነገርን እናገራለሁና ስሙ፤ ከከንፈሮቼም ቅን ነገርን አወጣለሁ፤
ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ፤ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ፤
ጴጥሮስም አፉን ከፈተና እንዲህ አለ፥ “እግዚአብሔር ለሰው ፊት እንደማያዳላ በእውነት አየሁ።
ጳውሎስም ይመልስላቸው ዘንድ አፉን ሊከፍት ወድዶ ሳለ አገረ ገዢው ጋልዮስ መልሶ አይሁድን እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ አይሁድ ሆይ፥ የበደላችሁ በደል ቢኖር፥ ወይም ሌላ በደል ቢኖርበት አቤቱታችሁን በሰማሁና ባከራከርኋችሁ ነበር።
ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ስለ ኢየሱስም ከዚያው መጽሐፍ ጀምሮ አስተማረው።
ለእኔም፦ ቃልን እንዲሰጠኝ፥ አፌንም ከፍቼ የወንጌልን ምሥጢር በግልጥ እንድናገር ጸልዩልኝ።