Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሐዋርያት ሥራ 8:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 ፊል​ጶ​ስም አፉን ከፈተ፤ ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከዚ​ያው መጽ​ሐፍ ጀምሮ አስ​ተ​ማ​ረው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ከዚሁም መጽሐፍ ክፍል ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌል ሰበከለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ፊልጶስም አፉን ከፈተ፤ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 ፊልጶስም ከዚህ የቅዱስ መጽሐፍ ክፍል ጀምሮ ስለ ኢየሱስ መልካሙን ዜና አበሠረው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 ፊልጶስም አፉን ከፈተ፥ ከዚህም መጽሐፍ ጀምሮ ስለ ኢየሱስ ወንጌልን ሰበከለት።

Ver Capítulo Copiar




ሐዋርያት ሥራ 8:35
20 Referencias Cruzadas  

እር​ሱም ከሙ​ሴና ከነ​ቢ​ያት፥ ከመ​ጻ​ሕ​ፍ​ትም ሁሉ ስለ እርሱ የተ​ነ​ገ​ረ​ውን ይተ​ረ​ጕ​ም​ላ​ቸው ጀመር።


ተሰ​ብ​ስ​በው ሳሉም በሕ​ዝቡ ሁሉ ፊት አይ​ሁ​ድን በግ​ልጥ እጅግ ይከ​ራ​ከ​ራ​ቸው ነበር፤ ስለ ኢየ​ሱ​ስም እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ከመ​ጻ​ሕ​ፍት ማስ​ረጃ ያመ​ጣ​ላ​ቸው ነበር።


ከተ​ሰ​ቀ​ለው ከኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በቀር በእ​ና​ንተ ዘንድ ሌላ ነገር እሰ​ማ​ለሁ ብዬ አል​ጠ​ረ​ጠ​ር​ሁም ነበር።


ከዚ​ህም በኋላ ወደ እርሱ የሚ​መ​ጡ​በ​ትን ቀን ቀጠ​ሩ​ትና ብዙ​ዎች ወዳ​ረ​ፈ​በት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥ​ዋ​ትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እየ​መ​ሰ​ከረ ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱ​ስም ከሙሴ ኦሪ​ትና ከነ​ቢ​ያት እየ​ጠ​ቀሰ ነገ​ራ​ቸው።


አፉንም ከፍቶ አስተማራቸው እንዲህም አለ፦


ሁል​ጊ​ዜም በቤተ መቅ​ደ​ስና በቤት ስለ ጌታ​ችን ስለ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ እንደ ሆነ ማስ​ተ​ማ​ር​ንና መስ​በ​ክን አል​ተ​ዉም።


በር​ግጥ ከሰ​ማ​ች​ሁት፥ እው​ነት በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ነውና እው​ነ​ትን በእ​ርሱ ዘንድ ትማ​ራ​ላ​ችሁ፤


የቆ​ሮ​ን​ቶስ ሰዎች ሆይ፥ ለእ​ና​ንተ አፋ​ችን የተ​ከ​ፈተ ነው፤ ልባ​ች​ንም የሰፋ ነው።


እኛ ግን የተ​ሰ​ቀ​ለ​ውን ክር​ስ​ቶ​ስን እን​ሰ​ብ​ካ​ለን፤ ይህም ለአ​ይ​ሁድ ማሰ​ና​ከያ ለአ​ሕ​ዛ​ብም ስን​ፍና ነው።


ከአ​ይ​ሁ​ድም አስ​ማት እያ​ደ​ረጉ የሚ​ዞሩ ሰዎች ክፉ​ዎች መና​ፍ​ስት ባሉ​ባ​ቸው ላይ “ጳው​ሎስ በሚ​ያ​ስ​ተ​ም​ር​በት በኢ​የ​ሱስ ስም እና​ም​ላ​ች​ኋ​ለን” እያሉ የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ስም ይጠ​ሩ​ባ​ቸው ነበር።


ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ወደ አን​ጾ​ኪያ ሄደው ለአ​ረ​ማ​ው​ያን የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ነገር ያስ​ተ​ማሩ የቆ​ጵ​ሮ​ስና የቄ​ሬና ሰዎች ነበሩ።


ጴጥ​ሮ​ስም አፉን ከፈ​ተና እን​ዲህ አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት እን​ደ​ማ​ያ​ዳላ በእ​ው​ነት አየሁ።


ወዲ​ያ​ው​ኑም “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ነው” ብሎ ስለ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በየ​ም​ኵ​ራ​ቦቹ ሰበከ፥ አስ​ተ​ማ​ረም።


ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘን​ድም የይ​ቅ​ርታ ዘመን ይመ​ጣል። አስ​ቀ​ድሞ የመ​ረ​ጠ​ው​ንም ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ይል​ክ​ላ​ች​ኋል።


የኤ​ፌ​ቆ​ሮ​ስን ትም​ህ​ርት ከተ​ማሩ ፈላ​ስ​ፋ​ዎች መካ​ከ​ልና ረዋ​ቅ​ያ​ው​ያን ከሚ​ባ​ሉት ወገን የሆኑ ሌሎች ፈላ​ስ​ፎ​ችም የተ​ከ​ራ​ከ​ሩት ነበሩ፤ እኩ​ሌ​ቶ​ችም፥ “ይህ ለፍ​ላፊ ምን ሊና​ገር ይፈ​ል​ጋል?” ይሉ ነበር፤ ሌሎ​ችም፥ “ስለ ኢየ​ሱስ ከሙ​ታን ስለ መነ​ሣ​ቱም ሰብ​ኮ​ላ​ቸ​ዋ​ልና የአ​ዲስ አም​ላክ ትም​ህ​ር​ትን ያስ​ተ​ም​ራል” አሉ።


ጃን​ደ​ረ​ባ​ውም ለፊ​ል​ጶስ መልሶ፥ “ነቢዩ ስለ ማን እን​ዲህ ይላል? ስለ ራሱ ነውን? ወይስ ስለ ሌላ? እባ​ክህ ንገ​ረኝ” አለው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios