ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
ማቴዎስ 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወዲያውኑ ጀልባቸውንም ሆነ አባታቸውን ትተው ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም ወዲያውኑ ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም ወዲያውኑ ጀልባዋንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ወዲያው ታንኳይቱንና አባታቸውን ትተው ተከተሉት። |
ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም፤ ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም።
ከዚያም እልፍ ብሎ ሌሎችን ሁለት ወንድማማች የዘብዴዎስን ልጅ ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ከአባታቸው ከዘብዴዎስ ጋር በታንኳ መረባቸውን ሲያበጁ አየ፤ ጠራቸውም።
“ወደ እኔ የሚመጣ፥ ሊከተለኝም የሚወድ አባቱንና እናቱን፥ ሚስቱንና ልጆቹን፥ ወንድሞቹንና እኅቶቹን፥ የራሱንም ሰውነት እንኳ ቢሆን የማይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
እንግዲህ እንደዚሁ ከእናንተ ወገን ከሁሉ ያልወጣ፥ የእርሱ ገንዘብ ከሆነውም ሁሉ ያልተለየ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።