ማቴዎስ 27:65 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጲላጦስም “ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ፤” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም፣ “ጠባቂዎች አሏችሁ፤ ሄዳችሁ በምታውቁት መንገድ አስጠብቁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጲላጦስም “ጠባቂዎች አሉላችሁ፤ ሄዳችሁ እንደምታውቁት አስጠብቁ፤” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጲላጦስም “እነሆ፥ የሚጠብቁ ወታደሮች አሉአችሁ፤ ሂዱና በምታውቁት ዐይነት አስጠብቁ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጲላጦስም፦ ጠባቆች አሉአችሁ፤ ሄዳችሁ እንዳወቃችሁ አስጠብቁ አላቸው። |
እንግዲህ ደቀ መዛሙርቱ መጥተው በሌሊት እንዳይሰርቁት ለሕዝቡም ‘ከሙታን ተነሣ፤’ እንዳይሉ፥ የኋለኛይቱ ስሕተት ከፊተኛይቱ ይልቅ የከፋች ትሆናለችና መቃብሩ እስከ ሦስተኛ ቀን ድረስ እንዲጠበቅ እዘዝ፤” አሉት።