ማቴዎስ 27:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጲላጦስም በቅናት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቅናት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ያለበት ምክንያት ኢየሱስን በቅናት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ስለ ነበር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቅንዓት አሳልፈው እንደ ሰጡት ያውቅ ነበርና። |
እኔ ድካምን ሁሉና የብልሃት ሥራውን ተመለከትሁ፥ ለሰውም በባልንጀራው ዘንድ ቅንአትን እንዲያስነሣ አየሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።
አቤቱ፥ ከፍ ያለች ክንድህን አላወቁም፤ ካወቁ ግን ያፍራሉ። አላዋቆች ሰዎችን ቅንአት ያዛቸው፤ አሁንም እሳት ጠላቶችን ትበላለች።
እርሱም በፍርድ ወንበር ተቀምጦ ሳለ ሚስቱ “ስለ እርሱ ዛሬ በሕልም እጅግ መከራ ተቀብያለሁና በዚያ ጻድቅ ሰው ምንም አታድርግ፤” ብላ ላከችበት።