በቀትርም ጊዜ ቴስብያዊው ኤልያስ፥ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት ይጫወት ይሆናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል” እያለ ይዘባበትባቸው ጀመር።
ማቴዎስ 26:45 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ “እንግዲህስ ተኙ፤ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም ዐርፋችሁ ተኝታችኋል? እነሆ፤ ሰዓቱ ቀርቧል፤ የሰው ልጅ በኀጢአተኞች እጅ ዐልፎ ይሰጣል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ወደ ደቀመዛሙርቱ መጥቶ እንዲህ አላቸው “ከእንግዲህስ ተኙ፥ ዕረፉም፤ እነሆ ሰዓቱ ቀርቦአል፤ የሰው ልጅም በኀጢአተኞች እጅ ተላልፎ ይሰጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ወደ ደቀ መዛሙርቱ ተመልሶ መጣና እንዲህ አላቸው፤ “አሁንም ገና ተኝታችኋልን? ዕረፍትም እያደረጋችሁ ነውን? እነሆ፥ የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ ተላልፎ የሚሰጥበት ሰዓቱ ደርሶአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያ ወዲያ ወደ ደቀ መዛሙርቱ መጥቶ፦ እንግዲህስ ተኙ ዕረፉም፤ እነሆ፥ ሰዓቲቱ ቀርባለች የሰው ልጅም በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ይሰጣል። |
በቀትርም ጊዜ ቴስብያዊው ኤልያስ፥ “አምላክ ነውና በታላቅ ቃል ጩኹ፤ ምናልባት ይጫወት ይሆናል፥ ወይም አሳብ ይዞት ይሆናል፥ ወይም ተኝቶ እንደ ሆነ መቀስቀስ ያስፈልገዋል” እያለ ይዘባበትባቸው ጀመር።
አንተ ጐበዝ፥ በጕብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጕብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ፥ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፤ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ ዕወቅ።
እርሱም “ወደ ከተማ ከእገሌ ዘንድ ሄዳችሁ ‘መምህር ጊዜዬ ቀርቦአል፤ ከደቀ መዛሙርቴ ጋር ከአንተ ዘንድ ፋሲካን አደርጋለሁ ይላል’ በሉት፤” አለ።
ዘወትርም ከእናንተ ጋር በቤተ መቅደስ ስኖር እጃችሁን እንኳ አልዘረጋችሁብኝም፤ ነገር ግን ጊዜያችሁ ይህ ነው፤ የጨለማው አበጋዝም ሥልጣኑ ይህ ነው።”
“አሁንስ ነፍሴ ታወከች፤ ግን ምን እላለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍሴን አድናት፤ ነገር ግን ስለዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደርሻለሁ።
ከፋሲካ በዓል አስቀድሞ ጌታችን ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ወደ ላከው ወደ አብ ይሄድ ዘንድ ጊዜው እንደ ደረሰ ባወቀ ጊዜ በዓለም ያሉትን የወደዳቸውን ወገኖቹን ፈጽሞ ወደዳቸው።
ጌታችን ኢየሱስም ይህን ነገር ተናግሮ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አነሣና እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ፥ ሰዓቱ ደርሶአልና ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤