ማቴዎስ 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተቀብለውም ‘እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፤ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው፤’ ብለው በባለቤቱ ላይ አንጕኦራጕኦሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክፍያውን ሲቀበሉ በባለቤቱ ላይ በማጕረምረም፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተቀበሉም ጊዜ በባለቤቱ ላይ አጉረመረሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ገንዘቡን ተቀበሉና በወይኑ አትክልት ባለቤት ላይ እንዲህ እያሉ አጒረመረሙ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተቀብለውም፦ እነዚህ ኋለኞች አንድ ሰዓት ሠሩ፥ የቀኑንም ድካምና ትኩሳት ከተሸከምን ከእኛ ጋር አስተካከልሃቸው ብለው በባለቤቱ ላይ አንጕኦራጕኦሩ። |
ጻፎችና ፈሪሳውያንም፥ “ከቀራጮችና ከኃጥኣን ጋር ለምን ትበላላችሁ? ትጠጡማላችሁ?” ብለው በደቀ መዛሙርቱ ላይ አንጐራጐሩ።
ጌታችን ኢየሱስም ደቀ መዛሙርቱ ስለዚህ ነገር እንደ አንጐራጐሩ በልቡ ዐወቀባቸውና እንዲህ አላቸው፥ “ይህ ያሰናክላችኋልን?
እነዚህ እንደ ምኞታቸው እየሄዱ የሚያንጎራጉሩና ስለ ዕድላቸው የሚያጕረመርሙ ናቸው፤ እንዲረባቸውም ለሰው ፊት እያደሉ አፋቸው ከመጠን ይልቅ ታላቅ ቃል ይናገራል።