“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
ማቴዎስ 19:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባትህንና እናትህንአክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አባትህንና እናትህን አክብር፤ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባትህንና እናትህን አክብር፤ ጐረቤትህን እንደ ራስህ አድርገህ ውደድ፤ የሚሉት ትእዛዞች ናቸው” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባትህንና እናትህን አክብር፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። |
“አባትህንና እናትህን አክብር፤ መልካም እንዲሆንልህ፥ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድርም ዕድሜህ እንዲረዝም።
አትበቀል፤ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝና።
እርሱም መልሶ፥ “እግዚአብሔር አምላክህን በፍጹም ልብህ፥ በፍጹም ሰውነትህ፥ በፍጹም ኀይልህ፥ በፍጹም ዐሳብህ ውደደው፤ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ ይላል” አለው።
በኦሪት እንዲህ ብሎአልና፥ “አታመንዝር፤ አትግደል፤ አትስረቅ፤ በሐሰት አትመስክር፥ አትመኝ፤” ደግሞ ሌላ ትእዛዝ አለ፤ ነገር ግን የሁሉም ራስ “ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለው ነው።
እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ አባትህንና እናትህን አክብር፤ እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ላይ ዕድሜህ እንዲረዝም፥ መልካምም እንዲሆንልህ።