ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በግዞት አኑሩት፤ የመከራም እንጀራ መግቡት፤ የመከራም ውኃ አጠጡት በሉአቸው” አለ።
ማቴዎስ 18:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አልወደደም፤ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ነገር ግን ሊታገሠው ፈቃደኛ ስላልነበረ፣ ያለበትን ዕዳ እስኪከፍለው ድረስ ወህኒ ቤት አስገባው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ ግን አልፈለገም፤ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ ሄዶ በወኅኒ አሳሰረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውየው ግን እምቢ አለው። እንዲያውም ይዞት ሄደና ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወህኒ ቤት አሳሰረው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አልወደደም፥ ግን ሄዶ ዕዳውን እስኪከፍል ድረስ በወኅኒ አኖረው። |
ንጉሡ እንዲህ ይላል፦ በደኅና እስክመለስ ድረስ ይህን ሰው በግዞት አኑሩት፤ የመከራም እንጀራ መግቡት፤ የመከራም ውኃ አጠጡት በሉአቸው” አለ።