ለባሪያህ በአደረግኸው በምሕረትህና በእውነትህም ሁሉ በጎውን አድርግልኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።
ማቴዎስ 15:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም “አዎን ጌታ ሆይ! ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ፤” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷም፣ “አዎን ጌታ ሆይ፤ ውሾችም እኮ ከጌታቸው ማእድ የወዳደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም “አዎን ጌታ ሆይ! ነገር ግን ቡችሎችም ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “ጌታ ሆይ! እርግጥ ነው፤ ነገር ግን ውሾችም ከጌቶቻቸው ማእድ የሚወድቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም፦ አዎን ጌታ ሆይ፤ ቡችሎችም እኮ ከጌቶቻቸው ማዕድ የወደቀውን ፍርፋሪ ይበላሉ አለች። |
ለባሪያህ በአደረግኸው በምሕረትህና በእውነትህም ሁሉ በጎውን አድርግልኝ፤ በትሬን ብቻ ይዤ ይህን ዮርዳኖስን ተሻግሬ ነበርና፥ አሁን ግን የሁለት ክፍል ሠራዊት ሆንሁ።
ታስቢ ዘንድ፥ ታፍሪም ዘንድ፥ ደግሞም ስላደረግሽው ነገር ሁሉ ይቅር ባልሁሽ ጊዜ፥ስለ ኀፍረትሽ አፍሽን ትከፍቺ ዘንድ አይቻልሽም፤” ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
ቀራጩ ግን ራቅ ብሎ ቆመ፤ ዐይኖቹንም ወደ ላይ ወደ ሰማይ ሊያነሣ አልወደደም፤ ደረቱንም እየመታ፦ ‘አቤቱ፥ እኔን ኀጢኣተኛውን ይቅር በለኝ’ አለ።
አይሁዳዊንና አረማዊን አልለየም፤ አንዱ ጌታ የሁሉ ጌታ ነውና፥ እግዚአብሔር ባለጸጋ ስለሆነ ለለመነው ሁሉ ይበቃልና።
አንደበት ሁሉ ይዘጋ ዘንድ፥ ዓለምም ሁሉ ከእግዚአብሔር ፍርድ በታች ይሆን ዘንድ ኦሪት የሚናገረው ሁሉ በኦሪት ላሉት እንደ ተነገረ እናውቃለን።
መጽሐፍ፥ “በነገርህ ትጸድቅ ዘንድ፥ በፍርድህም ታሸንፍ ዘንድ” ብሎ እንደ ተናገረ እግዚአብሔር እውነተና ነውና፥ ሰውም ሁሉ ሐሰተና ነውና።
ከቅዱሳን ሁሉ ለማንስ ለእኔ የማይመረመረውን የክርስቶስን ባለጸግነት ለአሕዛብ አስተምር ዘንድ ይህን ጸጋ ሰጠኝ።