እግዚአብሔርም አለ፥ “በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀንና በሌሊትም ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች፥ ለዘመናት፥ ለዕለታት፥ ለዓመታትም ይሁኑ።
ማቴዎስ 15:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና፤” አሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ደቀ መዛሙርትህ የአባቶችን ወግ የሚተላለፉት ለምንድን ነው? ምግብ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡም” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ደቀ መዛሙርትህ ለምን የሽማግሌዎችን ልማድ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና” አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ደቀ መዛሙርትህ የሽማግሌዎችን ወግ ስለምን ያፈርሳሉ? እነሆ! ምግብ የሚበሉት እጃቸውን ሳይታጠቡ ነው!” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርትህ ስለ ምን የሽማግሎችን ወግ ይተላለፋሉ? እንጀራ ሲበሉ እጃቸውን አይታጠቡምና አሉት። |
እግዚአብሔርም አለ፥ “በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ፥ በቀንና በሌሊትም ይለዩ ዘንድ ብርሃናት በሰማይ ጠፈር ይሁኑ፤ ለምልክቶች፥ ለዘመናት፥ ለዕለታት፥ ለዓመታትም ይሁኑ።
ፈሪሳውያንና ጻፎችም “ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ወግ ስለ ምን አይሄዱም? ነገር ግን እጃቸውን ሳይታጠቡ እንጀራ ይበላሉ፤” ብለው ጠየቁት።
ለዚህ ዓለም ስሕተት፥ በክርስቶስ ሕግ ያይደለ፥ በሰው ሠራሽ ሥርዐት ለከንቱ የሚያታልሉ ሰዎች በነገር ማራቀቅ እንዳያታልሉአችሁ፥ ተጠንቀቁ።
ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።