ንጉሡም ኢዮአቄም፥ ሠራዊቱ ሁሉ፥ አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፤ ኡርያም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ፤ ወደ ግብፅም ገባ።
ማቴዎስ 14:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሄሮድስም ዮሐንስን ሊገድለው ፈልጎ ነበር፤ ሕዝቡ ግን እንደ ነቢይ ይመለከተው ስለ ነበር ፈራ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊገድለው ይፈልግ ነበር፥ ነገር ግን ሕዝቡ እንደ ነቢይ ያዩት ስለ ነበር ፈራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ሄሮድስ ዮሐንስን ሊገድለው ይፈልግ ነበር፤ ነገር ግን የአይሁድ ሕዝብ እንደ ነቢይ ያዩት ስለ ነበር ሕዝቡን ፈራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊገድለውም ወዶ ሳለ፥ ሕዝቡ እንደ ነቢይ ስለ አዩት ፈራቸው። |
ንጉሡም ኢዮአቄም፥ ሠራዊቱ ሁሉ፥ አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፤ ኡርያም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ፤ ወደ ግብፅም ገባ።
ዮሐንስ በጽድቅ መንገድ መጥቶላችሁ ነበርና፤ አላመናችሁበትም፤ ቀራጮችና ጋለሞቶች ግን አመኑበት፤ እናንተም ይህን አይታችሁ ታምኑበት ዘንድ በኋላ ንስሐ አልገባችሁም።
እነርሱንም የሚቀጡበት ምክንያት ስለ አጡባቸው ገሥጸው ለቀቁአቸው፤ ስለ ተደረገው ተአምር ሕዝቡ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑ ነበርና።
ከዚህም በኋላ የቤተ መቅደሱ ሹም ከሎሌዎቹ ጋር ሔዶ አባብሎ አመጣቸው፤ በግድም አይደለም፤ በድንጋይ እንዳይደበድቧቸው ሕዝቡን ይፈሩ ነበርና።