ወደ ታንኳይቱም በወጡ ጊዜ ነፋሱ ተወ።
ኢየሱስና ጴጥሮስ ጀልባው ላይ እንደ ወጡ ነፋሱ ጸጥ አለ።
ወደ ጀልባዋ በወጡ ጊዜ ነፋሱ ፀጥ አለ።
ኢየሱስና ጴጥሮስ ወደ ጀልባው በገቡ ጊዜ ነፋሱ ጸጥ አለ።
ወዲያውም ኢየሱስ እጁን ዘርግቶ ያዘውና “አንተ እምነት የጎደለህ፤ ስለምን ተጠራጠርህ?” አለው።
በታንኳይቱም የነበሩት “በእውነት የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” ብለው ሰገዱለት።
እጅግም ፈሩና “እንግዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።
ወደ እነርሱም ወደ ታንኳይቱ ገባ፤ ነፋሱም ተወ፤ እነርሱ ራሳቸው ያለ መጠን እጅግ ተገረሙ፤
ወደ ታንኳውዪቱ ሊያወጡት ሲሹም ታንኳዪቱ ወዲያውኑ ሊሄዱ ወደ ወደዱበት ወደብ ደረሰች።