ማቴዎስ 14:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ “ምትሐት ነው” ብለው ታወኩ፤ በፍርሃትም ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደቀ መዛሙርቱም በባሕሩ ላይ ሲራመድ ባዩት ጊዜ ፈሩ፤ እነርሱም፣ “ምትሀት ነው!” በማለት በፍርሀት ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደቀመዛሙርቱ በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ “ምትሐት ነው” ብለው ደነገጡ፤ ከፍርሃትም የተነሣ ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደቀ መዛሙርቱም በባሕሩ ላይ እየተራመደ ሲሄድ ባዩት ጊዜ በጣም ፈርተው ደነገጡ፤ “ይህ ምትሐት ነው!” ብለውም በፍርሃት ጮኹ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደቀ መዛሙርቱም በባሕር ላይ ሲሄድ ባዩት ጊዜ፦ ምትሐት ነው ብለው ታወኩ በፍርሃትም ጮኹ። |
እነርሱም “አብደሻልን? አንድ ጊዜ ታገሺ” አሉአት፤ እርስዋ ግን እርሱ እንደ ሆነ ታረጋግጥ ነበር። እነርሱም፥ “ምናልባት መልአኩ ይሆናል” አሉ።