ከይሁዳም አለቆችና ታላላቆች ጋር ተከራከርሁና እንዲህ አልኋቸው፥ “ይህ የምታደርጉት ክፉ ነገር ምንድን ነው? የሰንበትንስ ቀን ታረክሳላችሁን?
ማቴዎስ 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኀጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይስ ካህናት ሰንበትን ሽረው በቤተ መቅደስ ውስጥ ሥራ ቢሠሩ በደል እንደማይሆንባቸው ከኦሪት ሕግ አላነበባችሁም? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰንበታት በቤተ መቅደስ ያሉ ካህናት ሰንበትን እንደሚያረክሱ ንጹሐንም እንደ ሆኑ በሕጉ አላነበባችሁምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞስ ካህናት በሰንበት ቀን በቤተ መቅደስ ሰንበትን ሲጥሱ በደል ሆኖ እንደማይቈጠርባቸው በሙሴ አማካይነት በተሰጠው ሕግ የተጻፈውን አላነበባችሁምን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካህናትም በሰንበት በመቅደስ ሰንበትን እንዲያረክሱ ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው በሕጉ አላነበባችሁምን? |
ከይሁዳም አለቆችና ታላላቆች ጋር ተከራከርሁና እንዲህ አልኋቸው፥ “ይህ የምታደርጉት ክፉ ነገር ምንድን ነው? የሰንበትንስ ቀን ታረክሳላችሁን?
ለእስራኤል ቤት ተናገር፤ እንዲህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ የኀይላችሁን ትምክሕት፥ የዐይናችሁን አምሮት፥ የነፍሳችሁንም ምኞት፥ መቅደሴን አረክሳለሁ፤ ያስቀራችኋቸውም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ በሰይፍ ይወድቃሉ።