ማቴዎስ 11:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀንበሬ ልዝብ፤ ሸክሜም ቀሊል ነውና።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀንበሬ ልዝብ፣ ሸክሜም ቀላል ነውና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀንበሬ ልዝብ፥ ሸክሜም ቀላል ነውና።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀንበሬ ልዝብ ነው፤ ሸክሜም ቀላል ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና። |
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?
በእኔም ሰላምን እንድታገኙ ይህን ነገርኋችሁ፤ በዓለም ግን መከራን ትቀበላላችሁ፤ ነገር ግን ጽኑ፤ እኔ ዓለሙን ድል ነሥቼዋለሁና።”
አሁንም እግዚአብሔርን አትፈታተኑት፤ እኛም አባቶቻችንም ልንሸከመው ያልቻልነውን ቀንበር በደቀ መዛሙርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭናላችሁ?
ሥርዐት እንዳናከብድ ሌላም ሸክም እንዳንጨምር መንፈስ ቅዱስ ከእኛ ጋር ነውና፤ ነገር ግን ይህን በግድ ትተዉ ዘንድ እናዝዛችኋለን።