ማቴዎስ 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመንገዳችሁም ከረጢት፣ ትርፍ እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ የዕለት ጕርሱ ይገባዋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመንገዳችሁ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሠራተኛ ምግቡ የሚገባው ስለ ሆነ ለመንገዳችሁ ከረጢት፥ ትርፍ እጀ ጠባብ፥ ትርፍ ጫማ፥ በትርም አትያዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይም ለመንገድ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አታግኙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና። |
እንዲህም አላቸው፥ “በትርም ቢሆን፥ ከረጢትም ቢሆን፥ እንጀራም ቢሆን፥ ወርቅም ቢሆን፥ ሁለት ልብስም ቢሆን ለመንገድ ምንም አትያዙ።
ዳዊትም በትሩን በእጁ ያዘ፤ ከወንዝም አምስት ድብልብል ድንጋዮችን መረጠ፤ በእረኛ ኮሮጆውም በኪሱ ከተታቸው፤ ወንጭፍም በእጁ ነበረ፤ ወደ ፍልስጥኤማዊውም ቀረበ።
ሳኦልም አብሮት ያለውን ብላቴና፥ “እነሆ! እንሄዳለን፤ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ሰው ምን እንወስድለታለን? እንጀራ ከከረጢታችን አልቆአልና፤ ለእግዚአብሔር ሰው የምንወስድለት ምንም የለንም” አለው።