ማርቆስ 9:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ “በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ?” ብሎ ጠየቃቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። ቤት ከገባ በኋላም፣ “በመንገድ ላይ የምትከራከሩት ስለ ምን ነበር?” ብሎ ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ወደ ቅፍርናሆም መጡ። ቤት ከገባ በኋላም፥ “በመንገድ ላይ የምትከራከሩት ስለምን ነበር?” ብሎ ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ወደ ቅፍርናሆም መጡ፤ ኢየሱስ ወደ ቤት ከገባ በኋላ ደቀ መዛሙርቱን፦ “በመንገድ ሳላችሁ የተከራከራችሁበት ነገር ምን ነበር?” ሲል ጠየቃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ቅፍርናሆምም መጣ። በቤትም ሆኖ፦ በመንገድ እርስ በርሳችሁ ምን ተነጋገራችሁ? ብሎ ጠየቃቸው። |
ሦስተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ ጴጥሮስም ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ስላለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “እንኪያስ ግልገሎችን ጠብቅ” አለው።
እኛን በሚቈጣጠር በእርሱ በዐይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቈተና የተገለጠ ነው እንጂ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።
ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ ኵላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።