ማርቆስ 8:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ገና አላስተዋላችሁምን?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “እስከ አሁን አላስተዋላችሁም ማለት ነውን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም፥ “እስከ አሁን አላስተዋላችሁም ማለት ነውን” አላቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “ታዲያ፥ ገና አታስተውሉምን?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገና አላስተዋላችሁምን? አላቸው። |
ጌታችን ኢየሱስም እንዲህ አለው፥ “ፊልጶስ፥ ይህን ያህል ዘመን አብሬአችሁ ስኖር አታወቀኝምን? እኔን ያየ አብን አየ፤ እንግዲህ እንዴት አብን አሳየን ትላለህ?
ይህንም የምላችሁ ስዘልፋችሁ ነው፤ እንግዲህ ከመካከላቸሁ ወንድማማቾችን ከወንድሞቻቸው ጋር ማስታረቅ የሚችል ሽማግሌ የለምን?