ፀሓይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አትዩኝ፤ የእናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፤ ነገር ግን የእኔን የወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
ማርቆስ 4:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፤ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፀሓይ በወጣ ጊዜ ግን ጠወለገ፤ ሥር ባለመስደዱም ደረቀ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፤ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ ፀሐይ በወጣ ጊዜ ጠወለገ፤ የጠለቀ ሥር ስላልነበረውም ደረቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀሐይም ሲወጣ ጠወለገ፥ ሥርም ስላልነበረው ደረቀ። |
ፀሓይ መልኬን አክስሎታልና ጥቁር ስለ ሆንሁ አትዩኝ፤ የእናቴ ልጆች ስለ እኔ ተጣሉ፥ የወይን ቦታዎችንም ጠባቂ አደረጉኝ፤ ነገር ግን የእኔን የወይን ቦታ አልጠበቅሁም።
ለተዋረዱ ሰዎች ከተሞች ረዳት ሆነሃልና፥ በችግራቸው የተጨነቁትን በደስታ ጋረድሃቸው፤ ከክፉዎች ሰዎችም አዳንሃቸው፤ ለተጠሙት ጥላ ሆንሃቸው፤ ለተገፉትም ሕይወት ሆንሃቸው።
ፀሐይም በወጣች ጊዜ እግዚአብሔር ትኩስ የምሥራቅ ነፋስን አዘዘ፤ ዮናስንም እስኪዝል ድረስ ፀሐይ ራሱን መታው፤ ለራሱም ተስፋ ቈርጦ፥ “ከሕይወት ሞት ይሻለኛል” አለ።
ፀሐይ ከትኵሳት ጋር ይወጣልና፥ ሣርንም ያጠወልጋልና፥ አበባውም ይረግፋልና፥ የመልኩም ውበት ይጠፋልና፤ እንዲሁ ደግሞ ባለ ጠጋው በመንገዱ ይዝላል።
እነዚህ ከእናንተ ጋር ሲጋበዙ በፍቅር ግብዣችሁ እንደ እድፍ ናቸው፤ እንደ እረኞች ያለ ፍርሃት ራሳቸውን ይጠብቃሉ፤ በነፋስ የተወሰዱ ውሃ የሌለባቸው ደመናዎች፥ ፍሬ የማያፈሩ ሁለት ጊዜ የሞቱ ከነሥራቸው የተነቀሉ በበጋ የደረቁ ዛፎች፥