ማርቆስ 3:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዴት ትልቅ ነገርም እንዳደረገ ሰምተው ብዙ ሰዎች ከይሁዳ ከኢየሩሳሌምም ከኤዶምያስም ከዮርዳኖስ ማዶም ከጢሮስና ከሲዶና ምድርም ወደ እርሱ መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሚሠራውን ነገር የሰሙ ሰዎችም ከይሁዳ፣ ከኢየሩሳሌም፣ ከኤዶምያስ፣ በዮርዳኖስ ማዶ ካለው አገር እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ ወደ እርሱ መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያደረገውን ነገር ሁሉ ሰምተው፥ ከኢየሩሳሌም፥ ከኤዶምያስ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ፥ ከጢሮስና ከሲዶና አካባቢ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያደርግ የነበረውንም ነገር ሁሉ በሰሙ ጊዜ ብዙ ሰዎች ተከተሉት፤ እነርሱም ከገሊላ፥ ከይሁዳ፥ ከኢየሩሳሌም፥ ከኤዶምያስ፥ ከዮርዳኖስ ማዶ ካለው አገር፥ እንዲሁም ከጢሮስና ከሲዶና ከተሞች የመጡ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዴት ትልቅ ነገርም እንዳደረገው ሰምተው ብዙ ሰዎች ከይሁዳ ከኢየሩሳሌምም ከኤዶምያስም ከዮርዳኖስ ማዶም ከጢሮስና ከሲዶና ምድርም ወደ እርሱ መጡ። |
የእስራኤል ቤት ርስት ባድማ ስለ ሆነ በላዩ ደስ እንዳለህ፥ እንዲሁ አደርግብሃለሁ፤ የሴይር ተራራ ሆይ! አንተና መላው ኤዶምያስ ባድማ ትሆናላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃለህ።”
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ያሳድዱአትና ይበዘብዙአት ዘንድ በልባቸው ሁሉ ደስታና በነፍሳቸው ንቀት ምድሬን ርስት አድርገው ለራሳቸው በሰጡ በቀሩት አሕዛብና በኤዶምያስ ሁሉ ላይ በቅንአቴ እሳት ተናግሬአለሁ፤
“ወዮልሽ ኮራዚ! ወዮልሽ ቤተ ሳይዳ! በእናንተ የተደረገው ተአምራት በጢሮስና በሲዶና ተደርጎ ቢሆን፥ ማቅ ለብሰው አመድም ነስንሰው ከብዙ ጊዜ በፊት ንስሐ በገቡ ነበርና።
ከእነርሱም ጋር ወርዶ በሰፊ ቦታ ቆመ፤ ከደቀ መዛሙርቱም ወገን ብዙ ሰዎች ነበሩ፤ ከመላው ይሁዳና ከኢየሩሳሌም፥ ከጢሮስና ከሲዶና ባሕር ዳርቻ ትምህርቱን ሊሰሙ፥ ከደዌአቸውም ሊፈወሱ የመጡት ከሕዝቡ ወገን እጅግ ብዙዎች ነበሩ።
በደቡብም በኩል በምድራቸው ዳርቻ እስከ ኤዶምያስ ድንበር ያሉት የይሁዳ ልጆች ነገድ ከተሞች እነዚህ ነበሩ፤ ቤሴሌኤል፥ አራ፥ አሦር፤