ማርቆስ 3:33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልሶም “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው?” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም መልሶ፣ “እናቴ ማን ናት፣ ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” ሲል ጠየቃቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም “እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነማን ናቸው?” ሲል መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልሶም፦ እናቴ ማን ናት? ወንድሞቼስ እነ ማን ናቸው? አላቸው። |
ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።
ስለዚህ ከአሁን ጀምሮ በሥጋ የምናውቀው የለም፤ ክርስቶስንም በሥጋ ብናውቀው አሁን ግን ከእንግዲህ ወዲህ የምናውቀው አይደለም።
እናቱንና አባቱን አላየኋችሁም ላለ፥ ወንድሞቹንም ላላወቀ፥ ልጆቹንም ላላስተዋለ፤ ቃልህን ለጠበቀ፥ በቃል ኪዳንህም ለተማጠነ።