ማርቆስ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርኵሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” እያሉ ጮኹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርኩሳን መናፍስትም ባዩት ቍጥር ከፊቱ እየወደቁ፣ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ” በማለት ይጮኹ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርኩሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤” እያሉ ጮኹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርኩሳን መናፍስትም ሲያዩት በፊቱ እየተደፉ፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ!” እያሉ ይጮኹ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርኵሳን መናፍስትም ባዩት ጊዜ በፊቱ ተደፍተው፦ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ እያሉ ጮኹ። |
“ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር” አለው።
ብዙ አጋንንትም፥ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ” እያሉና እየጮሁ ይወጡ ነበር፤ እርሱም ይገሥጻቸው ነበር፤ ክርስቶስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበርና እንዲናገሩ አይፈቅድላቸውም ነበር።
ጌታችን ኢየሱስንም ባየው ጊዜ ጮኸ፤ ሮጦም ሰገደለት፤ “የልዑል እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ሆይ፥ ካንተ ጋር ምን አለኝ?” እያለም በታላቅ ቃል ጮኸ፤ እንዳያሠቃየውም ማለደው።
ከዚህም በኋላ ጳውሎስንና እኛን እየተከተለች፥ “እነዚህ ሰዎች የልዑል እግዚአብሔር አገልጋዮች ናቸው፤ የሕይወትንም መንገድ ያስተምሩአችኋል” እያለች ትጮኽ ነበር።
መሰብሰባችሁ ለፍዳ እንዳይሆን፥ የተራበ ቢኖር በቤቱ ይብላ፤ አትነቃቀፉም፤ ሌላውን ሥርዐት ግን መጥቼ እሠራላችኋለሁ።