ማርቆስ 2:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም እንደ ተመለሰ፣ ወደ ቤት መግባቱን ሕዝቡ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ገባ፤ በቤት ውስጥ እንዳለም ተሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጥቂት ቀን በኋላ ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም ተመልሶ መጣ፤ እዚያ በቤት ውስጥ መሆኑ ተሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጥቂት ቀን በኋላ ወደ ቅፍርናሆም ደግሞ ገብቶ በቤት እንደ ሆነ ተሰማ። |
እርሱ ግን ሲወጣ ብዙ ሊሰብክና ነገሩን ሊያወራ ጀመረ፤ ስለዚህም ኢየሱስ ተገልጦ ወደ ከተማ መግባት ወደ ፊት ተሳነው፤ ነገር ግን በውጭ በምድረ በዳ ይኖር ነበር፤ ከየስፍራውም ወደ እርሱ ይመጡ ነበር።
እርሱም፥ “በውኑ ባለ መድኀኒት ራስህን አድን፤ በቅፍርናሆም ያደረግኸውንና የሰማነውን ሁሉ በዚህም በሀገርህ ደግሞ አድርግ ብላችሁ ይህችን ምሳሌ ትመስሉብኛላችሁ” አላቸው።
እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ከይሁዳ ወደ ገሊላ እንደ መጣ በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ ሄደ፤ ሊሞት ቀርቦ ነበርና ወርዶ ልጁን ያድንለት ዘንድ ለመነው፤
ይህንም ቃል ሲናገሩ ሰምተው ሁሉም ደንግጠው ተሰበሰቡ፤ ሁሉም በየሀገራቸው ቋንቋ ሲናገሩ ሰምተዋቸዋልና የሚሉትን አጡ።