ማርቆስ 16:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ ሕያው መሆኑንና ለርሷም መታየቱን ሲሰሙ አላመኗትም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ ግን አላመኗትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋ “ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ፥ በሕይወት አለ፤ እኔም በዐይኔ አይቸዋለሁ፤” ብላ ነገረቻቸው፤ እነርሱ ግን አላመኑአትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም ሕያው እንደ ሆነ ለእርስዋም እንደ ታያት ሲሰሙ አላመኑም። |
ሙሴም ይህን ለእስራኤል ልጆች ተናገረ፤ እነርሱ ግን ከሰውነታቸው መጨነቅ፥ ከሥራቸውም ክብደት የተነሣ ቃሉን አልሰሙትም።
ሌሎች ደቀ መዛሙርትም፥ “ጌታችንን አየነው” አሉት፤ እርሱ ግን፥ “የችንካሩን ምልክት በእጁ ካላየሁ፥ ጣቴንም ወደ ተቸነከረበት ካልጨመርሁ፥ እጄንም ወደ ጎኑ ካላገባሁ አላምንም” አላቸው።