ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
ካፌዙበት በኋላም ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ የገዛ ልብሱን አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
ካፌዙበትም በኋላ ቀዩን ልብስ አውልቀው፥ የራሱን ልብስ አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
ከተዘባበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፥ ልብሱንም አለበሱት፥ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
ከዘበቱበትም በኋላ ቀዩን ልብስ ገፈፉት፤ ልብሱንም አለበሱት፤ ሊሰቅሉትም ወሰዱት።
ራሱንም በመቃ መቱት፤ ተፉበትም፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት።
አንድ መንገድ አላፊም የአሌክስንድሮስና የሩፎስ አባት ስምዖን የተባለ የቀሬና ሰው ከገጠር ሲመጣ መስቀሉን ይሸከም ዘንድ አስገደዱት።
ከዚህ በኋላ ሊሰቅሉት አሳልፎ ሰጣቸው፤ ጌታችን ኢየሱስንም ተቀብለው ወሰዱት።