አባቱም ገሠጸው፤ እንዲህም አለው፥ “ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድን ነው? በውኑ እኔና እናትህ፥ ወንድሞችህም መጥተን በምድር ላይ እንሰግድልህ ይሆን?”
ማርቆስ 15:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም፣ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ እጅ ነሡት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም፥ “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፤ ሰላም ለአንተ ይሁን” እያሉ እጅ ነሡት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን!” እያሉ በማፌዝ እጅ ይነሡት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአይሁድ ንጉሥ ሆይ፥ ሰላም ለአንተ ይሁን እያሉ እጅ ይነሱት ጀመር፤ |
አባቱም ገሠጸው፤ እንዲህም አለው፥ “ይህ ያለምኸው ሕልም ምንድን ነው? በውኑ እኔና እናትህ፥ ወንድሞችህም መጥተን በምድር ላይ እንሰግድልህ ይሆን?”
ኑ፥ እንግደለውና በአንድ ጕድጓድ ውስጥ እንጣለው፤ ክፉ አውሬም በላው እንላለን፤ ሕልሞቹም ምን እንደሚሆኑ እናያለን።”
ከእሾህም አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ፥ በቀኝ እጁም መቃ አኖሩ፤ በፊቱም ተንበርክከው “የአይሁድ ንጉሥ ሆይ! ሰላም ለአንተ ይሁን፤” እያሉ ዘበቱበት፤